Mini vic.gov.au

This is a low bandwidth version of vic.gov.au. Contents may not be up to date. © Copyright State Government of Victoria

ሰው አክባሪ፣ ደህንነት የሚጠብቅ፣ ተሳታፊ፦ የተማሪን ባህሪ ለመደገፍ የሚያስፈልጉ የጋራ ፍላጎቶች (Shared expectations to support student behaviour) - አማርኛ (Amharic)

On this page

አንድ ላይ፣ ሁሉም ሰው የኔ ነው የሚላቸው፣ የሚማርባቸው እና የሚያድግባቸው ደህንነታቸው የተጠበቀ ትምህርት ቤቶችን እንፈጥራለን።

ትምህርት ቤቶች፣ ቤተሰቦች እና ተማሪዎች አብረው ሲሰሩ፣ የበለጠ ውጤት እናመጣለን። እነዚህ ሽርክናዎች/ግንኙነቶች ሁሉም ተማሪዎች የእኔነት ስሜት እንዲሰማቸው (እንዲቀላቀሉ)፣ እንዲማሩ እና እንዲያድጉ የሚረዱ የት/ቤት አካባቢዎችን ለመፍጠር አስፈላጊ ናቸው። እንደ ወላጅ እና ተንከባካቢ፣ ልጅዎ የሚጠበቅበትን የጋራ ባህሪ እንዲረዳ እና እንዲያሟላ በመርዳት ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።

ተማሪዎች የሚጠበቁ ባህሪያትን እንዴት እንደሚያሳዩ

በትምህርት ቤት፣ ሁሉም ተማሪዎች ሰው አክባሪ፣ ደህንነት የሚጠብቁ፣ እና ተሳታፊ እንዲሆኑ ይጠበቅባቸዋል። እነዚህ ባህሪያት ትምህርት ቤቶች ሁሉም ሰው ስኬታማ የሚሆንበት ቦታ ለማድረግ ይረዳሉ።

ተማሪዎች አክባሪደህንነት የሚጠብቁ እና ተሳታፊ በመሆን እነዚህን የሚጠበቁ የባህሪይ ፍላጎቶች ያሟላሉ።

ሰው አክባሪ

ደህንነት የሚጠብቅ

ተሳታፊ

ወላጆች እና ተንከባካቢዎች እንዴት መርዳት እንደሚችሉ

አወንታዊ ባህሪን ሞዴል/አርአያ ሆኖ በማሳየት እና በማበረታታት፣ ልጅዎ በትምህርት ቤት ስኬታማ ለመሆን የሚያስፈልጉትን ክህሎቶች እና ልምዶች እንዲገነባ ያግዛሉ። ቤተሰቦች እና ትምህርት ቤቶች አብረው ሲሰሩ፣ ተማሪዎች የበለጠ ውጤት ማምጣት ይችላሉ።

ወላጆች እና ተንከባካቢዎች የልጃቸውን ባህሪ እንደሚከተለው እንዲሆን በመደገፍ ሊረዱ ይችላሉ፡-

ሰው አክባሪ

ደህንነት የሚጠብቅ

ተሳታፊ

አንዳንድ ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው ትምህርት ቤት መገኘት ትግል ሊሆንባቸው እንደሚችል ወይም ወደ ትምህርት ቤት የመሄድ እምቢተኝነት ጋር እየታገሉ እንደሆነ እናውቃለን። ሊረዱ የሚችሉ አንዳንድ ግብዓቶች እነሆ፦

ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የሚጠበቅባችው ባህሪ እንዲያሟሉ እንዴት እንደሚደግፉ

አወንታዊ ባህሪን በማስተማር እና በማጠናከር፣ ትምህርት ቤቶች በመማር እና በደህንነት ላይ ያተኮረ አወንታዊ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ፍትሃዊ የመማሪያ አካባቢ እንዲኖሩ ያረጋግጣሉ።

ትምህርት ቤቶች ሰው አክባሪደህንነታቸው የተጠበቀ እና ተሳታፊ በመሆን ቤተሰቦችን እና ተማሪዎችን ይደግፋሉ።

ሰው አክባሪ

ደህንነት የሚጠብቅ

ተሳታፊ

የትምህርት መምሪያ አወንታዊ የተማሪ ባህሪን ለመገንባት እና በትምህርት ቤቶች፣ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች መካከል አወንታዊ ግንኙነቶችን ለማጎልበት ለትምህርት ቤቶች ግብዓቶችን እና ድጋፍን ይሰጣል።

ወላጆች እና ተንከባካቢዎች እርዳታ ለማግኘት ወዴት መሄድ እንደሚችሉ

የልጅዎ ጤንነት፣ ባህሪ ወይም ደህንነት የሚያሳስብዎት ከሆነ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፡-

የሚከተሉት ግብዓቶችም ይገኛሉ፡-

Education & training

Updated 27 March 2026



About the VIC Government

Grants and programs

Jobs and careers

Arts, culture and heritage

Business and the workplace

Communities

Education and training

Environment, water and energy

Finance and economy

Health and social support

Housing and property

Law and justice

Safety and emergencies

Science and technology

Sport and recreation

Traffic and transport

Working in the Victorian Government