የመዋእለ ሕጻናት ዕቃ/ኪንደር ኪት (Kinder Kits) - አማርኛ (Amharic)
ከ2025 ጀምሮ፣ በገንዘብ በተደገፈ የሶስት አመት የመዋዕለ ሕፃናት ፕሮግራም የተመዘገበ እያንዳንዱ ልጅ የመዋዕለ ሕጻናት ጥቅል ( የኪንደር ኪት) ለመቀበል ብቁ ነው።
ለቤተሰቦች መመሪያ

ስለ ኪንደር ኪትዎ (Kinder Kit)
ልጅዎን በጨዋታ ውስጥ ማሳተፍ ትምህርታቸውን እና እድገታቸውን ለመደገፍ ጥሩ መንገድ ነው። ወላጆች፣ ተንከባካቢዎች እና ቤተሰቦች የዚያ ጉዞ እጅግ በጣም አስፈላጊው አካል ናቸው።
ኪንደር ኪት (Kinder Kits) በመፅሃፍ፣ ትምህርታዊ መጫወቻዎች እና ለልጅዎ እና ለቤተሰብዎ በቤት ውስጥ እንዲዝናኑባቸው በተዘጋጁ እንቅስቃሴዎች የተሞሉ ናቸው።
እያንዳንዱ ኪንደር ኪት (Kinder Kit) በተለይም ለሶስት አመት ህጻናት እንዲሆኑ ተደርገው የተሰሩ እቃዎችን ያካትታል።

የቪክቶሪያ የመጀመርያ ዓመታት (የልጅነት) ትምህርት እና የእድገት ማዕቀፍ (Development Framework)
የልጅነት ጊዜ አስተማሪዎች እና ባለሞያዎች ልጅዎ እንዲያድግ እና እንዲማር ይደግፋሉ።
የመዋዕለ ሕፃናት መርሃ-ግብሮች የልጆችን ትምህርት እና እድገት ለመምራት የቪክቶሪያ የመጀመሪያ ዓመታት ትምህርት እና ልማት ማዕቀፍን (VEYLDF) ይጠቀማሉ።
በእርስዎ ኪንደር ኪት ውስጥ ያለው ነገር ሁሉ በVEYLDF ውስጥ ካሉት 1 ወይም ከዚያ በላይ ውጤቶች ጋር ይገናኛል።
- ማንነት
- መማር
- ማህበረሰብ
- የሐሳብ ልውውጥ ማድረግ
- ደህንነት
ቦርሳ
የኪንደር ኪት ቦርሳዎች እቃዎችን ለመሸከም እና ለመጫወት በየቀኑ ሊያገለግሉ ይችላሉ።
የትኛው ቦርሳ የእርሱ መሆኑን እንዲያውቅ፣ ልጅዎ ከኋላ ባለው የካርቶን መለያ ላይ ስዕል መሳል ይችላል።
የጀርባ ቦርሳውን ይክፈቱ እና ልሙጡን ገጽታ ለምናባዊ ጨዋታ ለመጠቀም የቬልክሮ ማጣበቂያውን ቦርሳው ውስጥ ይለጥፉ።

- ቦርሳው በልጅዎ ጀርባ ላይ እንዲሆን የቦርሳውን ማሰሪያዎችን ያጥብቁ ወይም ያላሉ
- በጨርቅ ማጣበቂያው ታሪክ ይፍጠሩ
- በስም መለያው ላይ መሳል ያበረታቱ
- የቅድመ-ጽሑፍ ችሎታዎችን ይለማመዱ
ማንበብ
ማንበብ እንደ ቤተሰብ አብሮ ጊዜ ለማሳለፍ ጥሩ መንገድ ነው። የማንበብ እና መጻፍ ክህሎትን ለማሳደግ ከሚረዱ በጣም አስፈላጊ መንገዶች አንዱ ነው።
ከልጅዎ ጋር መደበኛ የተረት-ተረት ጊዜን ማሳለፍ የልጅዎን ዐይነ ኅሊና እና የቃላት ስብስብ ለማዳበር ይረዳል።

- አንድ ላይ መጽሐፍ ይምረጡ
- ለመቀመጥ እና ለማንበብ ምቹ ቦታ ይፈልጉ
- በታሪኩ ውስጥ ቀጥሎ ምን ሊመጣ እንደሚችል ልጅዎን ይጠይቁ
- ከገጸ ባህሪያቱ ጋር ለማዛመድ በተለያየ ድምጽ ያንብቡ
መሳል እና ምልክት ማድረግ
ስዕል እና ምልክት ማድረግ ልጆች ሀሳባቸውን በፈጠራ እንዲገልጹ እና በራስ መተማመንን እንዲገነቡ ያስችላቸዋል። በወረቀት ላይ ክሬይኖችን በመሞከር፣ ልጆች፦
- እንዴት እንደሚጻፍ ለመማር ጠቃሚ የሆነውን ጥሩ የእንቅስቃሴ ክህሎቶችን ያዳብራሉ
- የእጆቻቸውን እና የዓይኖቻቸውን ቅንጅት ያሻሽላሉ
- ስለ ቀለሞች፣ ቅርጾች፣ ቅጦች እና መስመሮች ይማራሉ
- የፈጠራ ችሎታን ያሳያሉ
- ከሌሎች ጋር ሃሳብ ይለዋወጣሉ።

- ልጅዎን በመሳሉ ሂደት እንዲደሰት ያበረታቱት
- ልጅዎ ስለ ስዕሉ እንዲናገር ለማድረግ ግልጽ ጥያቄዎችን ይጠይቁ
- እርስዎ የሚያዩዋቸውን ቀለማት እና ቅርጾች ይሰይሙ
የፈጠራ እንቅስቃሴዎች
የፈጠራ ጨዋታ ሁሉንም 5 የልጅዎን ስሜቶች ያነቃቃል - ማየት፣ ማሽተት፣ መስማት፣ መዳሰስ እና ጣዕምን መለየት። በዙሪያዎ ያለውን አለም ለማሰስ፣ ለማግኘት እና ለመማር አስደሳች መንገድ ነው።

- ለልጅዎ እንደገና መጀመር ምንም ችግር እንደሌለው በማሳየት የመቋቋም ችሎታን ያበረታቱ። ብሎኮቹ ከወደቁ፣ ጥቂት ጥልቅ ትንፋሾችን ይተንፍሱ እና አብረው እንደገና ይገንቡ።
- የመጫወቻውን ሊጥ እንደ ኳስ ለማድቦልቦል ይሞክሩ፣ ቅርጾችን ይስሩ፣ ጠፍጣፋ ያድርጉት፣ ይጫኑት።
- አብረው ሙዚቃ ይስሩ። እጆችዎን በማጨብጨብ ወይም በቤት ውስጥ ያሉትን እቃዎች በመነካካት የተለያዩ ዜማዎችን እና ምቶች ይፍጠሩ።
የውጪ ጨዋታ
ክትትል የሚደረግበት የውጪ ጨዋታ የልጅዎ እድገት እና ደህንነት ትልቅ አካል ነው።
ልጆች የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፦
- ተፈጥሮን በመመልከት ስለ ሳይንስ ያላቸውን ግንዛቤ ያሳድጉ
- የነጻነት ስሜት ያግኙ
- ከሌሎች ልጆች ጋር ማህበራዊ ግንኙነት ማድረግ
- በሚጫወቱበት ጊዜ ጥሩ ምርጫዎችን ማድረግን ያስሱ እና ይማሩ
- መላውን የሰውነት እንቅስቃሴ፣ የእጅ-ዓይን ቅንጅት እና ትናንሽ የሰውነት ጡንቻዎች ቅንጅት እና እንቅስቃሴ እና የፈጠራ ችሎታዎችን ያዳብራሉ።

- ስለ ቅጠሎች ይናገሩ እና የተለያዩ ቀለሞችን እና ቅርጾችን ይሰይሙ
- ዘሮችን አንድ ላይ ይትከሉ
- ከተፈጥሮ ጋር ይገናኙ። አካባቢያችንን ስለመጠበቅ ይነጋገሩ
- የአሸዋ ቤተመንግስት ይገንቡ
ድራማዊ ጨዋታ
ድራማዊ ጨዋታ ልጆች ምናባዊ ታሪኮችን እንዲሰሩ እና የሌሎችን ገፀ-ባህሪያት ሚና እንዲጫወቱ ያበረታታል።
ልጆች ወሳኝ የሆኑ ቋንቋዎችን እና ማህበራዊ ክህሎቶችን ለመለማመድ ድራማዊ ጨዋታን ይጠቀማሉ፣ ይህም የሚከተሉትን ያካትታል፡-
- አዲስ ዓለምን ማሰስ እና መፍጠር
- ማጋራት እና ተራ መጠበቅ
- እርስ በርስ የመገናኘት እና የመደራደር መንገዶች።

- እንስሶቹን በእንግሊዝኛ እና በሌሎች ቋንቋዎች ይሰይሙ
- ገጸ ባህሪያትን ይፍጠሩ
- ታሪኮችን ይፍጠሩ
- አስተያየቶችን በተለይም የተለያዩ ስሜቶችን ለመመርመር እና ለመግለጽ እንስሳትን ይጠቀሙ
ጨዋታዎች
ከቤተሰብ እና ከጓደኞች ጋር ጨዋታዎችን መጫወት የልጅዎን ማህበራዊ ክህሎቶች ለመገንባት ጥሩ መንገድ ነው።
ጨዋታዎች ልጆች የቁጥር፣ የቋንቋ እና ችግር የመፍታት ክህሎቶችን እንዲማሩ ያግዛቸዋል።

- የጨዋታ ህጎችን ይማሩ እና ተራ በተራ መጫወት ይለማመዱ
- የችግር አፈታት እና የማስታወስ ችሎታዎችን ያጠናክሩ
- ቁጥሮችን ተወያዩ እና በእቃዎች መቁጠር ተለማመዱ
ማሕበረሰብ መገንባት
ጨዋታ፤ ልጆች ስለ ራሳቸው የሚያውቁበት እና በዙርያቸው ስላለው ዓለም የሚማሩበት መንገድ ነው። ለልጆች፣ መጫወትና መማር እጅ ለእጅ ተያይዘው የሚሄዱ ናቸው። በእርስዎ ኪንደር ኪት (Kinder Kit) ውስጥ ያሉት እቃዎች ስለ ብዝሃነት እና ስለተለያዩ ባህሎች ውይይቶች እንዲያደርጉ ይረዱዎታል።

- ስለ ሌሎች ሃገሮች እና ስለ የሃገራቸው እንስሳት ከልጅዎ ጋር ይነጋገሩ።
- የተለያዩ ቋንቋዎች ከየት እንደመጡ ለማየት የዓለምን ካርታ ይመልከቱ።
ማንነትን ማክበር
ልጆች ስለ ሁሉም ባህሎች እንዲማሩ ማበረታታት መግባባትን፣ ተቀባይነትን እና ኩራትን ይገነባል። የአቦርጂናል እና የቶረስ ስትሬት አይላንድ ባህሎች፣ እና እዚህ በቪክቶሪያ፣ የኩሪ ባህሎች፣ ዛሬ ያሉ እና በማደግ ላይ ያሉ ናቸው። በኪትስ ውስጥ እንደ ደራሲዎች እና አርቲስቶች እነሱን ለማክበር ኩራት ይሰማናል። ልጅዎ ስለ Koorie ወጎች እና ባህሎች የበለጠ እንዲያውቅ የሚያግዙ አንዳንድ ተግባራት እዚህ አሉ፦

- ለነገሮች ወይም እንስሳት የኩሪ ምልክቶችን ይማሩ
- ስለ ኮሪ ባህሎች፣ መሪዎች እና ጀግኖች ይማሩ እና ይናገሩ
- የሀገርን እውቅና አስፈላጊነት ይወቁ
በኣውስላን/Auslan የተጻፉ መጻሕፍት
አውስላን በቪክቶሪያ የቅድመ ልጅነት ቋንቋ ፕሮግራም ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውል የምልክት ቋንቋ ነው። ይህ መርሃ-ግብር በአንዳንድ መዋእለ ሕጻናት ውስጥ ይገኛል።
ልጆች ገና በለጋ እድሜያቸው ሌላ ቋንቋ ሲማሩ ብዙ ጥቅሞች አሉት፤ እነዚህም የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
- የቅድመ-ንባብ እና ቅድመ-ጽሑፍ ችሎታን መጨመር
- የተሻሻለ ተለዋዋጭ አስተሳሰብ
- ለራስ ከፍ ያለ ግምት እና ደህንነት
- የተጠናቀረ የባህል ማንነት።
በ ኪንደር ኪትስ ውስጥ የተካተቱት ብዙዎቹ መጽሃፍት ኦውስላን ትርጉሞች አሏቸው።

- ስሜቶችን በአውስላን በኩል ይግለጹ።
- በአውስላን ሰላም ይበሉ።
የልጆች ደህንነት፣ ህልውና እና ተጨማሪ ድጋፍ
ከልጆች ደህንነት እና ህልውና የበለጠ አስፈላጊ ነገር የለም። የልጆችን ደህንነት እንዴት እንደሚጠብቁ አገልግሎትዎን ይጠይቁ።
ሁሉም ልጆች የሚማሩት በተለያየ መንገድና በራሳቸው ፍጥነት ነው። የሚያሳስብዎት ነገር ካለ የቅድመ መዋእለ ህጻናት መምህርዎን ያነጋግሩ። እርስዎ ወይም ልጅዎ ተጨማሪ ድጋፍ ከፈለጉ፣ እገዛ በሚከተሉት መንገዶች ይገኛል፦

- ባልዎት ጥያቄዎች ላይ ለመወያየት ሀኪምዎን ወይም የእናትና ህጻን ጤና ጥበቃ ነርስን ለማየት ቀጠሮ ይያዙ
- ከተወለዱበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 6 አመት ዕድሜ የሆናቸው ልጆች ያሏቸው የቪክቶሪያ ቤተሰቦች በ13 22 29 በእናቶች እና ልጆች የጤና መስመር (Maternal and Child Health line) በቀን 24 ሰዓት በሳምንት 7 ቀናት ይደውሉ
በቅድመ ልጅነት ትምህርት ውስጥ ያሉ ሙያዎች
በቪክቶሪያ እያደገ ባለው የመዋዕለ ሕፃናት ዘርፍ ሥራ ለመጀመር ያስቡበት። እርስዎን የቅድመ ልጅነት መምህር ወይም አስተማሪ እንዲሆኑ ለመደገፍ፣ እነዚህ አሉ፦
- ተለዋዋጭ የጥናት አማራጮች
- ለጋስ ስኮላርሺፕ
- የገንዘብ ማበረታቻዎች።

የእርስዎን ኪንደር ኪት (Kinder Kit) በመለገስ ላይ
አንዴ ልጅዎ የኪንደር ኪት እቃዎቹን ከጨረሰ/ች በኋላ፣ እባክዎን በኃላፊነት ያስወግዷቸው።
እቃዎች በጥሩ ሁኔታ ላይ ከሆኑ፣ ለበጎ አድራጎት ድርጅት ለመለገስ ያስቡበት። እራስዎን ‘ይህን ለጓደኛዬ እሰጠዋለሁ?’ ብለው ጠይቁ። መልሱ አዎ ከሆነ፣ ለበጎ አድራጎት መለገስ ተገቢ ነው።
እቃዎችዎ ለመለገስ ተገቢ ካልሆኑ፣ እባክዎን በተቻለ መጠን እንደገና ጥቅም ላይ እንዲውሉ ያድርጉ።
ቆሻሻን በአግባቡ መቀነስ እና ማስወገድ ንፁህ እና አረንጓዴ ቪክቶሪያን ለመገንባት ይረዳል።

Updated 3 February 2026
About the VIC Government
- The Premier and ministers
- Find a Vic Gov department, agency or service
- Strategies and policies
- Inquiries and royal commissions
Grants and programs
Jobs and careers
Arts, culture and heritage
Business and the workplace
- Mentally Healthy Workplaces Framework
- Portable Long Service Authority
- Victoria’s racing industry
- Workforce Inspectorate Victoria
- Liquor licensing, sale and supply
Communities
- Children
- First Peoples - State Relations
- Finding records
- Gender equality & women’s leadership
- LGBTIQA+ equality
- Multicultural communities
- Seniors Online
- Veterans support and commemoration
- Volunteering in Victoria
- Youth Central
Education and training
- Victorian Early Childhood Regulatory Authority
- Early childhood education – information for professionals
- Kinder: Best Start, Best Life
- Education – information for parents
- Schools.Vic - information for schools
- Education grants, programs, awards and events
- PROTECT
- TAFE, training and universities sector
- TAFE Victoria
- Victorian Skills Authority
- Apprenticeships Victoria
- Learn Local
Environment, water and energy
Finance and economy
Health and social support
- Family violence reform
- NDIS Worker Screening Check
- NDIS and disability services and support in Victoria
- Patient Review Panel
- Transforming Trauma Victoria
Housing and property
Law and justice
- Adoption
- Births, deaths and marriages
- Honorary justices
- Machete ban
- Safeguarding Victorians against terrorism
- Stolen Generations Reparations Package
- Victims of Crime
- Victorian Racing Tribunal
Safety and emergencies
- Emergency Recovery Victoria
- Victorian Emergency Relief and Recovery Foundation
- Emergency Recovery Resource Portal
- How well do you know fire
- Fire Services Reform
- Water safety
- Marine Search and Rescue
Science and technology
- Data sharing and open data
- Data.vic - discover and access Vic Gov open data
- Developer.Vic - portal for API developers
- Go.vic URL shortener
- Vic Gov IT project dashboard
- Victoria’s free public wi-fi network
- Cyber security in the Victorian Government
Sport and recreation
Traffic and transport
- Cameras Save Lives
- Transport Fines
- Getting Around
- Transport Planning
- Transport Future
- Climate Change and transport
- Future Directions For Transport
- Transport projects
- Ports and Freight
Working in the Victorian Government
- Single Digital Presence home
- Accommodation and Library Services
- Executive employment in the Victorian public sector
- Budget, procurement and funding
- Careers in the Victorian Government
- Council and Regulator Toolkit
- Guidelines for working in government
- Join a government network
- Standards and guidelines
- VicFleet CarPool
- Victorian Government style guide