Mini vic.gov.au

This is a low bandwidth version of vic.gov.au. Contents may not be up to date. © Copyright State Government of Victoria

የቪክቶሪያ የፀረ ዘረኝነት ስትራቴጅ 2024–2029 (Victoria’s anti-racism strategy 2024-2029) - አማርኛ (Amharic)

ቪክቶሪያ ውስጥ የመጀመሪያው እና አጠቃላይ የመንግስት የፀረ-ዘረኝነት ስትራቴጂ በቪክቶሪያ ዘረኝነትን እና መድሎን ለማስቆም የሚያስችል የ5 ዓመት እቅድ ነው።

On this page

Victoria’s anti-racism strategy in Amharic PDF 1.17 MB (opens in a new window)

አብረን በመሥራት ሁሉንም አካታች የሆነ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ቪክቶሪያን መገንባት እንችላለን።

ዘረኝነት ምንድን ነው?

ዘረኝነት ማለት ሰዎች በማንነታቸውን ወይም በዘራቸውን ምክንያት የሚደርስባቸ አድልዎ እና በደል ነው። ማንቋሽሸን (ስድብን)፣ ማግለልን ወይም ከሌሎች ሰዎች ጋር እኩል የሆነ አጋጣሚ ወይም እድል አለመስጠትን ሊያካትት ይችላል።

ዘረኝነት በብዙ መንገዶች ሊከሰት ይችላል። ይህ ስትራቴጂ የሚያተኩረው ዘረኝነት በሚከተሉት ሁኔታዎች ውስጥ ሲከሰት ለመቅረፍ ነው፡

ራእያችን

ከዘረኝነትና ከአድልዎ ነጻ የሆነች ቪክቶሪያን መፍጠር። የዚህ መገለጫው ሁሉም ቪክቶሪያዊያን እኩል መብት፣ ነጻነትና ጥበቃ የሚያገኙበትና አስተማማኝ፣ ጤናማና ደጋፊ የሆኑ ማህበረሰቦች መገንባት ይሆናል።

ይህ ስትራቴጂ በቪክቶሪያ ውስጥ ዘረኝነትንና አድልዎ የመድረስ እድልን ለመቀነስ የሚያስችሉ 4 ግቦች አሉት፡

ይህንን ራእይ ለማሳካት

የፀረ-ዘረኝነት ስትራቴጅ የሚከተለውን ያከናውናል፡

ይህ ስትራቴጂ ዘረኝነትን በመቀነስ ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ እንገመግማለን እንዲሁም ያመጣውን ለውጥ ለህብረተሰቡ ሪፖርት እናደርጋለን።

ይህ ስትራቴጂ ለምን ያስፈልጋል?

ማህበረሰባችን የተቀላቀለ ነው

የዘር መድልዎ አሁንም ችግር ነው?

የመረጃ አለመኖር እና በማህበረሰብ አገልግሎቶች ላይ እምነት ማጣት ዘረኝነት በተገቢው ሁኔታ ሪፖርት እየተደረገ እንዳልሆነ መገመት ይቻላል።

ይህንን ችግር በተመለከት ከማን ጋር ውይይት አደረጋቹህ?

ከቀደምት ህዝቦች፤ ከባለብዙ ባህል እና ባለብዙ ሃይማኖት ማህበረሰባት ውስጥ የተወጣጡ ከ670 በላይ ቪክቶሪያውያን ጋር ተወያይተናል። በእነዚህ ውይይቶች ውስጥ የማህበረሰቡ መሪዎች፣ ባለሙያዎች እና ከማህበረሰቡ ጋር የስራ ግንኙነት ያላቸ ሠራተኞች ተካተውበታል።

ቪክቶሪያ ውስጥ ዘረኝነትን ሪፖርት ስለማድረግ

ማንም ሰው የዘረኝነት ጥቃት እየደረሰበት በዝምታ ማለፍ የለበትም። ቪክቶሪያ ውስጥ ዘረኝነትን ወይም የዘር አድልዎ ከደረሰብዎ ወይም ሌሎች ላይ ሲደርስ ካዩ ወደሚከተሉት አካላት ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ።

የቪክቶሪያ እኩል መብት እና የሰብአዊ መብት ኮሚሽን (Victorian Equal Opportunity and Human Rights Commission)

በሳምንቱ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 10ኤኤም እስከ 2ፒኤም ወደ 1300 292 153 ይደውሉ። ያለክፍያ በነጻ አስተርጓሚ ካስፈለገዎት ወደ 1300 152 494 ይደውሉ።

ኢሜይል enquiries@veohrc.vic.gov.au

በመስመር ላይ መደበኛ ያልሆነ ሪፖርት እዚህ ያድርጉ።

መስማት ለተሳናቸው፣ መስማት ለተቸገሩ ወይም የንግግር ችግር ካለብዎ ከብሄራዊ ቅብብሎሽ አገልግሎት (National Relay Service) ጋር ይገናኙ።

ቪክቶሪያ ፖሊስ

ድንገተኛ አደጋ ሲከሰት፣ ወንጀል እየተፈጸመ እንደሆነ ሪፖርት ለማድረግ ወይም ፖሊስ ወዲያውኑ በቦታው እንዲገኝ ወደ 000 ይደውሉ።

ድንገተኛ ላልሆኑ ጉዳዮች ወደ ፖሊስ እርዳታ መስመር 131 444 ላይ ይደውሉ ወይም ለነጻ አስተርጓሚ 131 450 ይደውሉ።

በአካባቢዎ ወደሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ ወይም በመስመር.ላይ ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ።

ማንነትዎን ሳይገልጹ ወደ ክራይም ስቶፐርስ (Crime Stoppers) 1800 333 000 ላይ በመደወል ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ።

ለተጨማሪ ድጋፍ እና ሪፖርት የማድረጊያ አማራጮችን ለማወቅ፤ እባክዎ የቪክቶሪያን የፀረ-ዘረኝነት ስትራቴጂን ድረ ገጽ ይጎብኙ።

ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ

ሙሉውን ስትራቴጂ በእንግሊዝኛ ወይም ይህንን መሳይ አጭር መግለጫ በሌሎች ቋንቋዎች መስመርላይ ማግኘት ይችላሉ።

ከክልሉ አስተዳዳሪ እና ካቢኔ ጽህፈት ቤት (Department of Premier and Cabinet ) የለበለጠ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ መጀመሪያ ወደ Translating and Interpreting Service (TIS) 131 450 ላይ ደውለው ወደ 03 9651 5111 እንዲደውሉልዎት መጠየቅ ይችላሉ።

በኢሜይል ወደ ክልሉ አስተዳዳሪ እና ካቢኔ ጽህፈት ቤት (Department of Premier and Cabinet ) antiracism.strategy@dpc.vic.gov.au መላክ ይችላሉ።

Communities

Updated 27 November 2024



About the VIC Government

Grants and programs

Jobs and careers

Arts, culture and heritage

Business and the workplace

Communities

Education and training

Environment, water and energy

Finance and economy

Health and social support

Housing and property

Law and justice

Safety and emergencies

Science and technology

Sport and recreation

Traffic and transport

Working in the Victorian Government