ነፃ መዋዕለ ህጻናት (ኪንደር) (About Free Kinder) - አማርኛ (Amharic)
On this page
- ለቤተሰቦች ቁጠባ
- የነጻ መዋዕለ ሕጻናት (ኪንደር) ብቁነት
- ነጻ መዋዕለ ሕጻናት (ኪንደር) የገንዘብ ድጋፍ እንዴት ማግኘት እንደሚቻል
- የክፍያው ማካካሻ ከኪስዎ ወጪ በሚደረጉ ክፍያዎች ላይ እንዴት እንደሚተገበር
ነፃ የመዋዕለ ህጻናት (ኪንደር) ኣገልግሎት በቪክቶሪያ ውስጥ ባሉ ተሳታፊ የአገልግሎት መስጫዎች ውስጥ ባሉ የሶስት እና የአራት-ዓመት መዋዕለ ህፃናት ወይም በቅድመ-ዝግጅት ፕሮግራሞች ውስጥ ይገኛል። ይህ ሁለቱንም የረጅም (ሙሉ) ቀን እንክብካቤ እና ራሱን የቻለ (የክፍለ ጊዜ ተብሎም ይጠራል) የመዋዕለ ህጻናት (ኪንደር) አገልግሎቶችን ያጠቃልላል።
ለቤተሰቦች ቁጠባ
በተሳታፊ ክፍለ-ጊዜ መዋእለ ህፃናት ውስጥ የተመዘገቡ ልጆች ያሏቸው ቤተሰቦች የነፃ ፕሮግራም ያገኛሉ።
በተሳታፊ የረጅም (የሙሉ) ቀን እንክብካቤ ውስጥ የተመዘገቡ ልጆች ያሏቸው ቤተሰቦች ዓመታዊ የክፍያ ማካካሻ ይቀበላሉ።
የነጻ መዋዕለ ሕጻናት (ኪንደር) ብቁነት
ነፃ መዋዕለ ሕጻናት (ኪንደር) ለሁሉም ሰው ነው።
ቤተሰቦች ለማግኘት ብቁ ለመሆን የጤና እንክብካቤ ካርድ ወይም የጡረታ ካርድ፣ የአውስትራሊያ ዜግነት ወይም የአድራሻ ማረጋገጫ ሊኖራቸው አይገባም። እንዲሁም ነፃ መዋዕለ ሕጻናት (ኪንደር) ለማግኘት ለአውስትራሊያ መንግሥት የሕጻናት እንክብካቤ ድጎማ (CCS) ብቁ መሆን አያስፈልግም።
ነጻ መዋዕለ ህጻናት (ኪንደር) መቀበል የሚችሉት ከአንድ መዋዕለ ህፃናት አገልግሎት ብቻ ነው። የመዋዕለ ሕጻናት (ኪንደር) አገልግሎት ነፃ መዋዕለ ሕጻናት (ኪንደር) የሚያገኙበትን አገልግሎት በመሰየም ደብዳቤ እንዲፈርሙ ይጠይቅዎታል። ልጅዎ ከአንድ በላይ የመዋዕለ ሕጻናት (ኪንደር) አገልግሎት የሚከታተል ከሆነ፣ ነፃ መዋዕለ ሕጻናት (ኪንደር)ን የት ማግኘት እንደሚፈልጉ ለእያንዳንዱ አገልግሎት ማሳወቅ አለብዎት።
ነጻ መዋዕለ ሕጻናት (ኪንደር) የገንዘብ ድጋፍ እንዴት ማግኘት እንደሚቻል
ነፃ መዋዕለ ሕጻናት (ኪንደር) የሚያቀርቡ የመዋዕለ ሕፃናት አገልግሎቶች በቀጥታ ከቪክቶሪያ መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ ያገኛሉ። ይህ ማለት ቤተሰቦች የሚመለስላቸው ገንዘብ እንደገና መጠየቅ አያስፈልጋቸውም ማለት ነው፣ ይልቁንስ ይህ ከሚከፍሉት ክፍያ ይቀነሳል። በክፍለ-ጊዜ መዋዕለ ህጻናት (ኪንደር) ፕሮግራሙ ነፃ ነው።
የረጅም ቀን እንክብካቤ መዋዕለ ህፃናት ፕሮግራሞችን የሚጠቀሙ ቤተሰቦች ከነጻ መዋዕለ ሕጻናት (ኪንደር) የሚገኘውን ቁጠባ በእያንዳንዱ የሂሳብ አከፋፈል ሂደት ‘የቪክቶሪያ መንግስት ነፃ መዋዕለ ህጻናት (ኪንደር) ማካካሻ’ በሚል በክፍያ መጠየቂያዎች ላይ በግልጽ ተሰይሞ ማየት ይችላሉ።
የክፍያው ማካካሻ ከኪስዎ ወጪ በሚደረጉ ክፍያዎች ላይ እንዴት እንደሚተገበር
የነፃ መዋዕለ ህጻናት (ኪንደር) ማካካሻ በዓመት ውስጥ በመደበኛነት በክፍያዎ ላይ ይካተታል (ለምሳሌ በየሳምንቱ ወይም በየሁለት ሳምንቱ)። በክፍያ መጠየቂያ (ኢንቮይስ) ላይ በግልጽ የተቀመጠውን መጠን ‘የቪክቶሪያ መንግሥት ነፃ መዋዕለ ህጻናት (ኪንደር) ማካካሻ’ በሚል ሥር ማየት መቻል አለብዎት።
ማካካሻው በክፍያዎ ላይ እንዴት እንደሚተገበር እና ይህ በክፍያ መጠየቂያዎ ላይ እንዴት እንደሚታይ መረጃ ለማግኘት እባክዎን ከመዋዕለ ሕፃናት አገልግሎትዎ ጋር በቀጥታ ይነጋገሩ። ልጅዎ በሳምንት ከ15 ሰአታት በላይ የሚጠቀም ከሆነ፣ እነዚህ ተጨማሪ ሰአታት በማካካሻ ክፍያው አይሸፈኑም።
ለአውስትራሊያ መንግሥት የሕጻናት እንክብካቤ ድጎማ (CCS) ብቁ ከሆኑ በመጀመሪያ ይተገበራል። ያ ማለት የአውስትራሊያ መንግሥት የሕጻናት እንክብካቤ ድጎማ (CCS) እና የነጻ መዋዕለ ህጻናት (ኪንደር) ማካካሻ ከተካተተ (ከተቀነሰ) በኋላ ብቻ ነው ቀሪውን መጠን መክፈል የሚያስፈልግዎት።
ለምሣሌ፦
- የ 4 ዓመት ልጅ በሳምንት ለ 3 ቀናት የመዋዕለ ህጻናት (ኪንደር) ፕሮግራም ወዳለው የረጅም (ሙሉ) ቀን እንክብካቤ መስጫ ከሄደ።
- አገልግሎቱ በሳምንት ለ3 ቀናት (የመዋዕለ ሕፃናት እና ተጨማሪ የእንክብካቤ ሰዓቶችን ጨምሮ) 360 ዶላር ያስከፍላል።
- ቤተሰቡ በሳምንት የ252 ዶላር ከአውስትራሊያ መንግሥት የሕጻናት እንክብካቤ ድጎማ (CCS) ያገኛል።
- ከ2026 ጀምሮ፣ አገልግሎቱ የ$2,101 ነፃ የመዋዕለ ሕጻናት ማካካሻ በየሳምንቱ ከ40 ሳምንታት በላይ (በሳምንት $52 አካባቢ) ይተገበራል።
- ቤተሰቡ ከሲሲኤስ (CCS) እና ነፃ መዋዕለ ሕጻናት (ኪንደር) ማካካሻ በኋላ በሳምንት 55 ዶላር አካባቢ ይከፍላል።
እባክዎን ያስታውሱ። ይህ ለምሳሌ ብቻ የተቀመጠ ነው፤ ወጪዎች ግን እንደየግለሰቡ ሁኔታ እና አመታዊ የነጻ ኪንደር ማካካሻ መጠን ይለያያል።
Updated 26 March 2026
About the VIC Government
- The Premier and ministers
- Find a Vic Gov department, agency or service
- Strategies and policies
- Inquiries and royal commissions
Grants and programs
Jobs and careers
Arts, culture and heritage
Business and the workplace
- Mentally Healthy Workplaces Framework
- Portable Long Service Authority
- Victoria’s racing industry
- Workforce Inspectorate Victoria
- Liquor licensing, sale and supply
Communities
- Children
- First Peoples - State Relations
- Finding records
- Gender equality & women’s leadership
- LGBTIQA+ equality
- Multicultural communities
- Seniors Online
- Veterans support and commemoration
- Volunteering in Victoria
- Youth Central
Education and training
- Victorian Early Childhood Regulatory Authority
- Early childhood education – information for professionals
- Kinder: Best Start, Best Life
- Education – information for parents
- Schools.Vic - information for schools
- Education grants, programs, awards and events
- PROTECT
- TAFE, training and universities sector
- TAFE Victoria
- Victorian Skills Authority
- Apprenticeships Victoria
- Learn Local
Environment, water and energy
Finance and economy
Health and social support
- Family violence reform
- NDIS Worker Screening Check
- NDIS and disability services and support in Victoria
- Patient Review Panel
- Transforming Trauma Victoria
Housing and property
Law and justice
- Adoption
- Births, deaths and marriages
- Honorary justices
- Machete ban
- Safeguarding Victorians against terrorism
- Stolen Generations Reparations Package
- Victims of Crime
- Victorian Racing Tribunal
Safety and emergencies
- Emergency Recovery Victoria
- Victorian Emergency Relief and Recovery Foundation
- Emergency Recovery Resource Portal
- How well do you know fire
- Fire Services Reform
- Water safety
- Marine Search and Rescue
Science and technology
- Data sharing and open data
- Data.vic - discover and access Vic Gov open data
- Developer.Vic - portal for API developers
- Go.vic URL shortener
- Vic Gov IT project dashboard
- Victoria’s free public wi-fi network
- Cyber security in the Victorian Government
Sport and recreation
Traffic and transport
- Cameras Save Lives
- Transport Fines
- Getting Around
- Transport Planning
- Transport Future
- Climate Change and transport
- Future Directions For Transport
- Transport projects
- Ports and Freight
Working in the Victorian Government
- Single Digital Presence home
- Accommodation and Library Services
- Executive employment in the Victorian public sector
- Budget, procurement and funding
- Careers in the Victorian Government
- Council and Regulator Toolkit
- Guidelines for working in government
- Join a government network
- Standards and guidelines
- VicFleet CarPool
- Victorian Government style guide